ክፍል 4: በኢትዮጵያ ወጣቶችን በመምከር እና ለአእምሮ ጤና ጉዳዮች ምላሽ በመስጠት ረገድ የመንፈሳዊ የምክክር አገልግሎት ሚና by Project dldl/ድልድል published on 2022-04-14T13:29:16Z እንኳን ወደ Project dldl/ድልድል ተከታታይ ፖድካስት በደህና መጡ። ይህ ተከታታይ ፖድካስት የተቋቋመው ህብረተሰቡን እና የሚመለከታቸውን አካላት በውይይቱ ላይ በማሳተፍ እና በሀገሪቱ ስላለው የቤት ውስጥ ጥቃት ግንዛቤ ለማስጨበጥ፣ ራሳችንን እና ሌሎችን በማስተማርና በዙሪያችን ያለውን ዝምታ ለመሰበር እውቀትና ግንዛቤ ያላቸው ሰዎች ተዛማጅ ርዕሶችን እንዲዳስሱ እና ግብዓቶችን እና አቅጣጫዎችን በማካፈል እነዚህን ልማዶች እና አስተሳሰቦች እንዲያሻሽሉ ለማድረግ ነው። በዚህ ክፍል ተጋባዥ እንግዳችን ቀሲስ ይግዛው መኮንን ናቸው። የፍኖት መስራች እና ዳይሬክተር ናቸው። የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በሥነ መለኮት እና የማስተርስ ዲግርያቸው ደግሞ በስነ ልቦና ሠርተዋል። ፍኖት የግዕዝ ቃል ሁኖ ትርጉሙ ደግሞ “መንገድ” ማለት ነው፡፡ ፍኖት ማህበራዊ እና ስነ ልቦናዊ የምክር በጎ አድራጎት ድርጅት ነው። የተቋቋመው ደግሞ ለተቸገሩ ሰዎች የማህበራዊ እና ስነ ልቦናዊ ተግዳሮቶችን ምላሽ የመስጠት ዓላማን ይዞ ነው። በዚህ ክፍል ቀሲስ ይግዛው ሃይማኖታዊ ትምህርትን በሥነ ልቦና ሕክምና ላይ ያለውን ጠቀሜታና ዉጤት እንድንረዳ ያብራራሉናል። የሃይማኖት ትምህርት እና ዘመናዊ የስነ-ልቦና ዜዴዎችን እንዴት እንደሚዋሃዱና፣ አዘውትረው የሚመጡት ደንበኞቻቸው እነማን እንደሆኑ እና በህክምናው ውስጥ የሚያግጥሙት በጣም የተለመዱ ጉዳዮች ላይ ስላለው የምክር ተሞክሯቸውን ያጫውተናል። Welcome to Project dldl/ድልድል podcast series. This podcast series was set up to engage in discussion the public and relevant groups in Ethiopia to promote awareness about domestic violence, to educate ourselves and others by having knowledgeable speakers explore related topics, and to share resources and directions to overcome norms that maintain silence around the problem in society. The series is hosted by Ms Etsegenet Hailemekeal, who is supporting the project with outreach and communications. For the purposes of accessibility, we will aim to alternate between English and Amharic. Our guest speaker in this episode is Kesis Yigzaw Mekonnen.He is the founder and director of Fnot. He holds his first degree in theology and his Masters in psychology. Fnot (meaning 'way') is a social and psychological counselling charitable organisation. It was established with the aim of responding to social and psychological challenges for people in need. In this episode, Kesis Yigzaw helps us to understand the importance and the effect of using religious teaching in psychological treatment. He also talks to us about his counselling experience on combining religious teaching and modern psychological techniques, his most frequent clients and the most common issues he faces in therapy. **We thank Tekeste Gebrenenya for allowing us to record him playing the traditional krar instrument and to use the audio in the podcast series.** Genre Religion & Spirituality