ክፍል 2፡ የቤት ውስጥ ጥቃትን ለመከላከል የሃይማኖት አባቶችን እና የእምነት ተዋናዮች ሚና by Project dldl/ድልድል published on 2022-03-25T11:22:01Z እንኳን ወደ Project dldl/ድልድል ተከታታይ ፖድካስት በደህና መጡ። ይህ ተከታታይ ፖድካስት የተቋቋመው ህብረተሰቡን እና የሚመለከታቸውን አካላት በውይይቱ ላይ በማሳተፍ እና በሀገሪቱ ስላለው የቤት ውስጥ ጥቃት ግንዛቤ ለማስጨበጥ፣ ራሳችንን እና ሌሎችን በማስተማርና በዙሪያችን ያለውን ዝምታ ለመሰበር እውቀትና ግንዛቤ ያላቸው ሰዎች ተዛማጅ ርዕሶችን እንዲዳስሱ እና ግብዓቶችን እና አቅጣጫዎችን በማካፈል እነዚህን ልማዶች እና አስተሳሰቦች እንዲያሻሽሉ ለማድረግ ነው። የዛሬው ዝግጅት እንግዳችን አቶ ባንታመላከ ገላው ይባላሉ፡፡ አቶ ባንተመላክ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የልማት ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ተጠባባቂ የጤና እና ማሕበራዊ ጉዳይ ኃላፊ ናቸው። በEOC-DICAC በፕሮጀክት በማስተባበርና ክትትል የ7 ዓመት ሥራ ልምድ አላቸው፡፡ የዚህ ኮሚሽን ተልእኮ በኢትዮጵያ የሚገኙ ተጠቂ ማሕበረሰቦች የድህነትን፣ ስደትን፣ የአየር ንብረት ለውጥን፣ የሕብረተሰብ ጤና ግንዛቤ ማነስን መንስኤዎችን በመታገል ዘላቂ የልማት ፕሮግራሞችን በማስተዋወቅ ራሳቸውን እንዲችሉ መርዳት ነው። አቶ ባንታምላክ ኮሚሽኑ በቤት ውስጥ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመፍታት ስለሚሰራባቸው የተለያዩ መንገዶች፣ ከመንግስት እና ከሌሎች አካላት ጋር ተባብሮ መስራት እና ከአለማዊ እና እምነት ተኮር ተቋማት ጋር ስንሠራ ሊያጋጥሙን ስለሚችሉ ተግዳሮቶች ይነግሩናል። ለተደራሽነት ዓላማ ሲባል በእንግሊዝኛ እና በአማርኛ እየቀያየርን የምናቀርብ ይሆናል፡፡ Welcome to Project dldl/ድልድል podcast series. This podcast series was set up to engage the public and relevant groups in the discussion and promote awareness about domestic violence in the country, to educate ourselves and others by having knowledgeable speakers explore related topics and to share resources and directions to overcome norms that maintain silence around the problem around us. For the purposes of accessibility, we will aim to alternate between English and Amharic. Our guest speaker on today's episode is Ato Bantamalake Gelaw, acting Head of Health & Social affairs at the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Development & Inter-Church Aid Commission. He has 7 years experience in project coordinating and monitoring at EOC-DICAC. The mission of this commission is to assist the vulnerable communities in Ethiopia to attain self-reliance by tackling the root causes of poverty, migration, climate change, public health illiteracy problems by promoting sustainable development programmes. Ato Bantamlake will be talking to us about the various ways the commission works to address domestic violence, the impact of collaborating with the government and other entities and potential challenges that we might encounter while working with secular and faith-based institutions. For the purposes of accessibility, we will aim to alternate between English and Amharic. Genre Religion & Spirituality