ክፍል 3: በኢትዮጵያ የቤት ውሰጥ ጥቃት እና የፌሚኒሰቶች ንቅናቄ by Project dldl/ድልድል published on 2022-04-06T16:13:02Z እንኳን ወደ Project dldl/ድልድል ተከታታይ ፖድካስት በደህና መጡ። ይህ ተከታታይ ፖድካስት የተቋቋመው ህብረተሰቡን እና የሚመለከታቸውን አካላት በውይይቱ ላይ በማሳተፍ እና በሀገሪቱ ስላለው የቤት ውስጥ ጥቃት ግንዛቤ ለማስጨበጥ፣ ራሳችንን እና ሌሎችን በማስተማርና በዙሪያችን ያለውን ዝምታ ለመሰበር እውቀትና ግንዛቤ ያላቸው ሰዎች ተዛማጅ ርዕሶችን እንዲዳስሱ እና ግብዓቶችን እና አቅጣጫዎችን በማካፈል እነዚህን ልማዶች እና አስተሳሰቦች እንዲያሻሽሉ ለማድረግ ነው። በዚህ ክፍል ተጋባዥ እንግዳችን ሕይወት አበበ ከሴታዊት ንቅናቄ ውስጥ የኮምዩኒኬሽን ግንኙነት አስተዳዳሪ ነች። ሴታዊት በ2014 የተመሰረተ የጾታ እኩልነት ንቅናቄ ስትሆን የሴታዊት ንቅናቄ ዓላማ የኢትዮጵያን ፌሚኒዝም ለመረዳት እና በኢትዮጵያውያን ሴቶች እና ወንዶች መካከል በውይይት፣ ጥናትና ምርምር እኩልነት ላይ ያተኮረ ንቅናቄ ላይ ትሰራለች ። በዚህ ክፍል ሕይወት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የቤት ውስጥ ጥቃት በፌሚኒዝም አካሄድ እንድንረዳ ታግዘናለች። የሴታዊትን እንቅስቃሴዎች እና ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ፌሚኒስት ተቋም ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶች ታጫውታናለች። Welcome to Project dldl/ድልድል podcast series. This podcast series was set up to engage in discussion the public and relevant groups in Ethiopia to promote awareness about domestic violence, to educate ourselves and others by having knowledgeable speakers explore related topics, and to share resources and directions to overcome norms that maintain silence around the problem in society. The series is hosted by Ms Etsegenet Hailemekeal, who is supporting the project with outreach and communications. For the purposes of accessibility, we will aim to alternate between English and Amharic. Our guest speaker on this episode is Hiwot Abebe from the Setaweet Movement. She is the communication manager. Setaweet (meaning ‘of woman’ in Amharic) is a contemporary feminist movement founded in 2014. The Setaweet Movement aims to articulate Ethiopian feminism and creates the space for dialogue, research, and activism by Ethiopian women and men. In this episode, Hiwot will help us understand the feminist approach to domestic violence in Ethiopia. She will also talk to us about some of the projects that they are working on along with some challenges they face as feminist movement in Ethiopia. **We thank Tekeste Gebrenenya for allowing us to record him playing the traditional krar instrument and to use the audio in the podcast series.** Genre Religion & Spirituality